kingdom-mission.org - Home - Kingdom Mission Alliance

Description: መንግሥት (KINGDOM) ተልእኮ (MISSION) ቅንጅት (ALLIANCE) አማርኛ ማን እንደሆንን Kingdom Mission Alliance (KMA) በአሜሪካን አገር እ. አ.አ. በ 2022 ዓ. ም. የተቋቋመ የበጎ አድራጎት መንፈሳዊ ድርጅት ነው። የዚህ ድርጅት (KMA) ዋና ዓላማ በሰሜን አሜሪካ፥ በኢትዮጵያና በመላው ዓለም የሚገኙትን የኢትዮጵያና የኤርትራ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት መንፈሳዊ አንድነትን በማጎልበት፥ ስልታዊ ቅንጅትን በመፍጠርና ወንጌልን ለአሕዛብ ሁሉ በማድረስ የሰውን ሁለንተናዊ

Example domain paragraphs

Kingdom Mission Alliance (KMA) በአሜሪካን አገር እ . አ . አ . በ 2022 ዓ . ም . የተቋቋመ የበጎ አድራጎት መንፈሳዊ ድርጅት ነው። የዚህ ድርጅት (KMA) ዋና ዓላማ በሰሜን አሜሪካ፥ በኢትዮጵያና በመላው ዓለም የሚገኙትን የኢትዮጵያና የኤርትራ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት መንፈሳዊ አንድነትን በማጎልበት፥ ስልታዊ ቅንጅትን በመፍጠርና ወንጌልን ለአሕዛብ ሁሉ በማድረስ የሰውን ሁለንተናዊ ሕይወት ማገልገል ነው። KMA የሚለው ስያሜ እንደሚያመለክተው ይህ ድርጅት በሦስት ቃላት ላይ ትኩረት ያደርጋል። እነዚህም መንግሥት፥ ተልእኮና ቅንጅት ናቸው። 

Kingdom Mission Alliance (KMA) is a charitable Christian organization founded in the United States in 2022. The purpose of this organization (KMA) is to create spiritual unity among the Ethiopian and Eritrean evangelical churches in North America, Ethiopia and all over the world through tactical coordination in order to take the gospel to all nations and minister to the whole person. The acronym KMA stands and emphasizes three words: kingdom, mission and alliance. 

KMA ከራሳችን ድርጅት ይልቅ ለእግዚአብሔር መንግሥት ቅድሚያ እንድንሰጥ፥ በጊዜያዊውና በምድራዊው አጀንዳ ሳንጠመድ በዘላለማዊ አመለካከት መኖር እንድንችል፥ ጌታችን እንዳስተማረን በሰማይ ያለውን  የእግዚአብሔርን ፈቃድ በምድር እንድንፈጽምና እንድናስፈጽም፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት በሕዝቦች  ሁሉ መካከል ማስፋፋት እንድንችል ያሳስበናል። በተጨማሪም የእግዚአብሔር መንግሥት ከሁላችንም  ይበልጣል ብለን እናምናለን፥ ለዚህም መንግሥት ትኩረት ሰጥተን እንሠራለን። የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን  አንዲት መሆኗንና በክርስቶስ ያመንን ሁላችን ደግሞ የዚህች የአንዲት ቤተ ክርስቲያን አባላት መሆናችንን  እናምናለን።